#ከይርዜና:- የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተገኙበት “የኢትዮጵያን ይግዙ” የንግድ ሳምንት ኤክስፖ ተከፍቷል።
የኢትዮጵያን ይግዙ የንግድ ሳምንት ኤክስፖ 2017 ከዛሬ ነሐሴ 24 እስከ 29 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄድ ነው።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያዘጋጀው "የኢትዮጵያን ይግዙ" ሀገራዊ የንግድ ሳምንት ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ስድስት ቀናት በጥራት መንደር ይከናወናል።
የኢትዮጵያን ጸጋና ምርቶች የሚያስተዋውቅ ኤግዚቢሽን እና ባዛርም ይካሄዳል።
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የኢትዮጵያን ይግዙ ሀገራዊ የንግድ ኤክስፖውን መርቀው ከፍተዋል።
ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተመርተው ለኤግዚቢሽኑ የቀረቡ ሀገራዊ ምርቶችንም ጎብኝተዋል።
#keyirnews #Ethiopia #addisababa #dailyvlog